በአለም አቀፍ የወንጀል ፍርድቤት ለተፈፀሙት ጥሰቶች ለዓይነ ምስክሮችና ለተጠቂዎች የተዘጋጀ ዌብ-ፖርታል
የጦር ወንጆሎች፣ የዘር ማጥፋት ወይም በሰው ልጆች ላይ የተፈፀሙ ወንጀሎች ተጎጂ ወይም ምስክር
ከሆኑ እና መረጃዉን ለስዊዘርላንድ ፖሊስ ማስተላለፍ ከፈለጉ በዚህ ዌብ ፖርታል በኩል ቃልዎትን ማስፈር
ይቻላሉ::የእርስዎ መረጃ ለወንጀል ምርመራ በጣም ኣስፈላጊ ሊሆን ይችላል::
በሚከተሉት ጉዳዮች ተጎጂ/ሰለባ ወይም የዓይን ምስክር ከሆኑ፣-
- በመከላከያ ሰራዊት ወይም በጦር ሰራዊት አባላት የደረሰ አካላዊ ወይም ስለ ልቦናዊ እንገልት ( ማሰቃየት: አፈና: ማፈናቀል: አስገድዶ መድፈር: ዘረፋ:ባዮሎጂካልና ኬሚካል መሳርያ: ፈንጅ መጠቀምን ያካትታል) ::
- በሰላማዊ ሰዎች ወይም በማህበረሰብ ላይ ያነጣጠረ ቀጥታዊ ጥቃት (በአካል ላይ ጉዳት ወይም ግድያ ጨምሮ )::
- በሰላማዊ ሰዎች ንብረት ላይ የደረሰ ጥቃት ( አምቡላንሶችን: ሆስፒታሎችን: የባህል እቃዎችን ትምህርት ቤቶችን እና የሃይማኖት ቤቶችን ጨምሮ)::
- ትጥቅ በፈቱ በጦር ሰራዊት አባላት በነበሩ (ምርከኞች) ላይ ይደረሰ ግፍ::
እና ይህንን መረጃ ለስዊዘርላንድ ፖሊስ ለማስረጃነት ለማቅረብ ከተስማሙ እባክዎ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ይመልሱ::
ሰለ ተጎጂው ወይም የመስካሪ መረጃ
ሰለ ክስተቱ መረጃ
በጦር ወንጆሎች፣ በዘር ማጥፋት ወይም በሰው ልጆች ላይ በተፈፀሙ ወንጆሎች ተጎጂ/ሰለባ ወይም ምስከር ከሆኑ: በዛን ወቅት እርስዎ የት ነበሩ? እባክዎትን የደረሱት ጥቃቶችን የተተገበሩበት አገር ወይም አገሮችን ያመልክቱ:: ተጨማሪም የወንጀል ክስተቶቹ የተከሰቱባቸው ከተሞች ወይም ቦታዎችን ይንገሩን:: ወንጀል የተፈጸመባቸው ቦታ አድራሻ: የጎዳናውን ስም ወይንም አካባቢው ይጠቁሙ:: እባክዎት በተቻሎት መጠን ሁኔታውን በትክክል ለመግለፅ ይሞክሩ::
ስለ መልካም ትብብርዎ እናመሰግናለን::